በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት እ.ኤ.አ ከሚያዝያ 5-28/2024 በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ በሚገኘው የስታርት አፕ ኢትዮጵያ ኤግዚቢሽን መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የባለድርሻ አካላትን በሳይንስ፤ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች የቢዝነስ ጅማሮ (ስታርት አፕ) ዙሪያ ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮችን እያካሄደ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት እ.ኤ.አ በ20/04/2024 የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሶስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማለትም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፤ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ስለ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው የኢንኩቤሽን ማዕከላት አሰራር፤ አደረጃጀት እና አቅም ላይ ገለጻ አቅርበዋል፡፡
በሶስቱ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንቶች ከቀረበው ገለፃ በተጨማሪ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስለ ስታርት አፕ ሂደት እና ደረጃዎች አጠቃላይ ገለጻ ቀርቧል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ኢኖቬሽን እና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና የ.አ.ሳ.ቴ.ዩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ ተፈራርመዋል፡፡