Exciting News from ABIC2024!
ASTU hosts a five-day DAAD Alumni workshop
ASTU held a colorful Graduation Ceremony 2024
ASTU held a colorful Graduation Ceremony 2024
ASTU held a colorful Graduation Ceremony 2024
ASTU Alumni Association Inspires Graduating Class with Career Tips!
abrontphoto
በዘንድሮ አመት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረው የአብሮነት ቀን በአዳማ ሳይንስና ቴክሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሚቆዩ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዛሬዉ ዕለት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሊጂ ዩኒቨርሲቲ መዝናኛ ክበብ በቡና ጠጡ ዝግጅት የተከናወነ ሲሆን ፕሮግራሙ በነገው እለትም በማስ ስፖርት አጓጊ ዉድድሮች እና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ደምቆ ይቀጥላል፡፡ የቡና ጠጡ ፕሮግራሙ በተለያዩ ሁለት ቦታዎች የተካሄደ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች በመዝናኛ ክበብ እንዲሁም ተማሪዎች በአንፊ የመዝናኛ ሰፍራ አክብረውታል ፡፡
የዕለቱን መርሃግብር ያስተዋወቁት የዩኒቨርሲቲዉ የአስተዳደርና ልማት ም/ፐሬዚዳንት እና የዝግጅት ኮሚቴዉ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰለሞን ጥሩነህ ናቸዉ፡፡ ስነስነርአቱን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ በንግግራቸው ባስተላለፉት መልእክት መላውን የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለእለቱ እንኳን አደረሰን በማለት መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚከበረው በዚህ ዝግጅት ብዙሀነትን ከመስበክ ባሻገር ብዝሀነትን መኖርን መልመድ ይገባናል ብለዋል ፡፡ ንግግራቸውን በመቀጠልም ብዙሃነትን መኖር በሚል መሪ ቃል በሚከበረው በዚህ የአብሮነት ሳምንት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከ3000 በላይ ሰዎች በሚሳተፉባቸው ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ጠቁመው እስከአሁን የመጣንበትን መልካም የመከባባርና የአብሮነት ሂደት በማጠናከር ሁሉም የዩነቨርሲቲው ማህበረሰብ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል ፡፡

ዶክተር ለሚ አያይዘው እንደአብራሩት ኢትዮዮጵያ ለረዠም አመታት የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩባት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት እንዲሁም የተለያዩ ሀይማኖትና እምነት ተከታዮች ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር መሆኗን አስታውሰዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ትንሿ ሀገር እንደመሆኗ በመቃቃርና ግጭት የትም የማይደረስ መሆኑን አምነን እንደሀገርና እንደዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብም አብሮ መኖር ያስፈልጋል በማለት መልእክታቸውን አጠቃለዋል ፡፡

Media Gallery

  • 1.jpg
  • 1a.jpg
  • 2.jpg
  • 3.jpg
  • 3a.jpg
  • 3aa.jpg
  • 3b.jpg
  • 4.jpg
  • 5.jpg
  • 6.jpg
  • 7a.jpg
  • 8.jpg
  • 8a.jpg
  • 8aa.jpg
  • 8b.jpg
  • 8c.jpg
  • 8d.jpg
  • 8f.jpg
  • 8g.jpg
  • 8i.jpg
  • 8j.jpg
  • 9.jpg
  • 9a.jpg
  • 9aa.jpg
  • 9b.jpg
  • 9bb.jpg
  • 9c.jpg
  • 9d.jpg
  • 9f.jpg
  • 9g.jpg

ASTU Campuse Map

maps1

Contact us

International Relations and Corporate Communications
Office: +251 -22-211-3961,  Email: [email protected]
P.O.Box: 1888 Adama, Ethiopia
Office of Registrar  
Office: +251 -221-100001,  Email: [email protected]
P.O.Box: 1888 Adama, Ethiopia


   © 2020  Adama Science and Technology University